Ethio Technology is a reliable Website Design & Development, Software Development, ERP Implementation Solution, Networking solutions and SEO service, Network Design and Cable Installation, Computer and Accessories Maintenance, IT Constancy and Short-Term Online Training provider in Ethiopia. We provide custom web, software, multi-platform solutions for Enterprise and Startup companies in Ethiopia. We offer website design, web development, software development, ERP, online marketing, web hosting and web application development at fair market pricing with a quicker turnaround than most other web design companies. It is a function of our in-house skill set and the ability to leverage technology to meet a wide array of demands; we're great at what we do, and our efficiency allows us to price our work competitively.
Consultationላፕቶፕ፣ ዴስክቶፕ እና ታብሌቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት የዲዛይን ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አስታወቀ።
የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ለኤፍ.ኤም አዲስ 97.1 እንደተናገሩት፣ ይህ መደረጉ ዜጎች እና ተቋማት የኔትወርክ ቁሶችን በመሠረታዊነት እንዲገለገሉ ያስችላል።
አሁን ላይ ምርቱን ለማስጀመር በርካታ ሀገራትን ያሳተፈ የግብአት አቅርቦት ሰንሰለት እየተገነባ መሆኑንም ገልጸዋል።
ግብአቶቹ በከፊል ሀገር ውስጥ በከፊል ደግሞ ከውጭ የሚመረቱም ይሆናል ነው የተባለው።
ዲዛይኑ በሀገር ቤት መሐንዲሶች እየተሠራ ሲሆን ወደምርት ሲገባ እሴት እንደሚታከልበት እና በተመጣጣኝ ዋጋም ለገበያ እንደሚቀርብ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የዲጂታል ዓለም የመረጃ ልውውጥ ማረጋገጫ ሥርዓት (Public Key Infrastructure) በቀጣይ ዓመት ለመጀመር እየተሠራ ነው።
ለዚህ ሥራ የተመደበው 8 ሚሊዮን ዶላር በጀት ሲለቀቅ ሥራው ይተገበራል።
የሀብት እና የጊዜ ብክነትን የሚያስቀር የተቋማት ዲጂታል መረጃ ልውውጥ ሥርዓትም በዚህ ዓመት ተጠናቅቆ ቀጣይ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበር ይሆናል።
በአንድ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ በርካታ አገልግሎቶችን ለመስጠት የማስቻል ቴክኖሎጂ (single sign on) ቀጣይ ዓመት ሥራ እንደሚጀምርም ተገልጿል።
የዲጂታል ማንኛውም መረጃ እና ልውውጥ ደኅንነት እና ማረጋገጫን በመተግበር ባንኮች ደንበኛዎን ይወቁ (know your customer) የተሰኘ አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ።
በኃ/ሚካኤል አበበ
Leave A Comment